image
image
image
image
image

በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እምርታ" የተቀመጡ ግቦች ለማሳካት በስራ እድል ፈጠራና በሌማት ትሩፍት ስራዎችን ትኩረት መስራት እንደሚገባ ተገለፀ

ታህሳስ 16, 2018
የልደታ ክፍለ ከተማ የቀጣይ 90 ቀናት በመደመር መንግስት እይታ የተቀመጡ ግቦች በስራ እድል ፈጠራና ሌማት ትሩፋት የንቅናቅ እቅድ ከሚመለከታቸ ባለድርሻዎች አካላት የጋራ አደረገ ። የልደታ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ፍታለው ከፍያለው እንዳሉት የቀጣይ የዘጠና ቀናት እቅድን የስራ እድል ፈጠራና የሌማት ትሩፋት ለማሳካት ሁሉም በራስ መንፈስ ተነሳሽነት ስራዎች በመስራት የሚጠበቅብንን ሀላፊነት መወጣት ይገባዋል ብለዋል የስራ እድል መፍጠር የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚረጋገጥበት በመሆኑ ይህ ተግባር ላይ በፍጥነትና በትኩረት በመስራት ውጤት ማምጣት ይገባል ያሉት አቶ ፍታለው አያይዘው ንቅናቄውን ለማሳካት በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ ምክትል ስራ አስፈፃሚና ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አራርሳ ድሪባ እንዳሉት የቀጣይ የዘጠና ቀናት እቅድን ለማሳካትና ለተግባራዊነቱ ላይ ሁሉም የድርሻውን መወጣት አለበት ብለዋል ። በሚፈጠረው የስራ እድል ላይ 75% የወጣቶችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል ያሉት አቶ አራርሳ አያይዘው የሌማት ትሩፋት ላይም የተሰጠውን እቅድ በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አሰፋ ቶላ የማይሰሩ እጆች እንዳይኖሩ አዳዲስ ተጠቃሚዎችን በመፍጠር ስራዎችን በልዩ ትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል። ዜሮ ግቦች ላይ ተረጂነትን ለመቀነስ ስራን የሚያማርጥ እጆች እንዳይኖሩ በትኩረት መስራት መቻል አለብን በማለት አቶ አሰፋ ገልፀዋል። ስራዎችን ለማሳካት ስምሪታችንን በማስተካከልና በትኩረት በመምራት ስራዎች በውጤት መታጀብ እንዳለባቸው አንስተዋል። የመድረኩ ተሳታፊዎችም የስራ እድል ፈጠራና ለሌማት ትሩፍት ተግባራትን በንቅናቄ በመስራት የያዝነውን ግብ በጋራ ማሳካት ይገባናል ብለዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች