የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
የልደታ ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ጠንካራ የኮሙኒኬሽን ስርዓት በመዘርጋት በቂና የተሟላ መረጃ ያለው፤ በሁለንተናዊ እድገት ንቁ ተሳትፎ የሚያደርግ ህብረተሰብ በመፍጠር ከተማችን አዲስ አበባ የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት እንድትሆን ለማስቻል የበኩሉን ራዕይ ሰንቆ በመንቀሳቀስ ላይ ነው፡፡ ጽ/ቤቱ በአዋጅ ቁጥር 74/2014 ዓ/ም በተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መሰረት የተለያዩ የኮሙኒኬሽን አግባቦችን በመጠቀም ዘመናዊ፣ ግልጽ እና ፈጣን ምላሽ መስጠትን ባህሉ ያደረገ የኮሙኒኬሽን ስርዓት በመዘርጋት ላይ ይገኛል፡፡
የኮሙኒኬሽን ዘርፉን በማጠናከር በመንግስትና በህዝብ መካከል ጥራት ያለውና እና ለሁሉም ነዋሪ ተደራሽ የመረጃ ፍሰት እንዲኖር በማድረግ የህዝቡን ትክክለኛ የመረጃ ፍላጎት በማርካት ተሳትፎና ተጠቃሚነቱን ማሳደግ፣ የሀገራችንና የከተማዋን መልካም ገጽታ መገንባት እንዲሁም በዋና ዋና ሀገራዊና ከተማ አቀፋዊ አጀንዳዎች ላይ የጋራ መግባበትን መፍጠር የሚያስችል ተልዕኮ ይዞ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡
ጽ/ቤቱ በ2017 በጀት ዓመት በህዝብና ሚዲያ ግንኙነት ተግባራት ተግባቦት በመፍጠር የመረጃ ተደራሽነትን ማሳደግ፣ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር ማድረግ፣ የዲጅታል ሚዲያ፣ ሞኒተሪንግ እና የከሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ መረጃ አገልግሎት ስርዓትን ማሳደግ እና ተቋማዊ የማስፈፀም አቅም፣ የሀብት አጠቃቀምና የአገልግሎት አሰጣጥ አሰራርን ማሻሻል ማዕከል ያደረጉ ስትረቴጂክ ግቦች ቀርፆ ወደ ተግባር ገብቷል፡፡
በ2017 በጀት ዓመት በዕቅድ ያስቀመጣቸውን ተግባራት ለማከናወን ያለሰለሰ ጥረት አድርጓል፡፡ በዕቅድ ይዞ ያከናወናቸውን ተግባራት አፈፃፀም በየጊዜው በመገምገም የታዩ ጥንካሬዎችን ማስቀጠልና ክፍተቶችን በማረም ውጤታማ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ተቋሙ በ2017 በጀት ዓመት ውጤታማ ስራ እንዲሰራ ስትሰሩ ለነበራቹህ ሁሉ ምስጋናየ የላቀ ነው በቀጣይም ድጋፋቹህ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አደራ እላለሁ
ሲፈን ባዩ , የጽ/በቱ ኃላፊ
