image
image
image
image
image

'የኮሙኒኬሽን ስራዎቻችንን በማጠናከር የክፍለ ከተማዋን ገጽታ በመገንባት ልማትን እናፋጥናለን'' ወ/ሮ ሲፈን ባዩ- የልደታ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ

ሀምሌ 10, 2018
ኮሙኒኬሽን የመንግስትንና የህብረተሰብን ተሳትፎ አጉልቶ በማውጣትና በማስተባበር በኩል ስኬታማ ስራዎች መሠራት በመቻሉ ጥራቱን የጠበቀ መረጃን በፍጥነት ለማህበረሰቡ ተደራሽ በመደረጉ ሀሰተኛ መረጃን መቀነስ ተችሏል ሲል የልደታ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ገለጸ። የልደታ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት የ2017 በጀት አመት አፈፃፀምና የ2018 መነሻ እቅድ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አደረገ የልደታ ክፍለ ከተማ የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ሲፈን ባዩ በበጀት አመቱ የመንግስትንና የማህበረሰብን ተሳትፎ አጉልቶ በማውጣትና በማስተባበር ስኬታማ ስራዎች መሠራቱን በመግለፅ የ2017 በጀት አመት የማህበረሰብ እና በመንግስት ተሳትፎ የተፈቱ የመልካም አስተዳደር ተግባራትን በተለያዩ የኮሙኒኬሽን አግባቦች በመጠቀም ተደራሽ ማድረግ ተችሏል በማለት ገልፀዋል። ጽ/ቤቱ እቅዱን መነሻ በማድረግ የተከናወኑ ስራዎች እንዳሉ በማንሳት በዘርፉ ለበርካታ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ስኬታማነት የላቀ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ተናግረዋል የኮሙኒኬሽን ተቋማት የመረጃ አያያዝና አደረጃጀት ይበልጥ በማጠናከርና በማሻሻል ፈጣን የመረጃ ልውውጥ እንዲኖር ያግዘናል ያሉት ወ/ሮ ሲፈን በበጀት አመቱ ግቦችንና ተግባራትን በተቀመጠው እቅዶች ልክ በወጥነት ማከናወን መቻሉ ገልፀዋል ። የተለያዩ የሀሰተኛ መረጃዎች በማሰራጨት ህብረሰቡ እንዳይረጋጋና ሀገሪቷም ሰላሟንና ጸጥታዋን እንዳታረጋግጥ ተግዳሮት እየሆነ ይገኛል ያሉት ኃላፊዋ ጽ/ቤቱም ከተለያዩ የወረዳና የክ/ከተማ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በሚያደርሰው ትክክለኛ መረጃ የሀሰተኛ መረጃ እንዲቀንስ ማድረግ ተችሏል በቀጣይም የተሻለ መረጃን በጥራት በመስራት ለማህበረሰቡ ተደራሽ እናደርጋለን ብለዋል። የምናስተላልፋቸው መልዕክቶችም የህዝቡን የልማት ተሳትፎ የሚያጎለብቱ እና በመንግስትና በህዝብ መካከል ያለው የልማት ትስስር እንዲጠናከር የሚያደርጉ ሊሆን ይገባል ብለው የመረጃና የኮሙኒኬሽን ስራዎቻችን ለሃገርና ለትውልድ ግንባታ ለማዋል የዘርፉ አመራር፣ባለሙያዎችና ማህበረሰብ አንቂዎች ተግተው መስራት አለባቸው በማለት አክለው ገልፀዋል። በተያያዘም የተቋሙን ስራዎች በተሻለ በማቀናጀት ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን ተገቢውን ትኩረት በመስጠት በቅንጅትና በተግባቦት ጥራት ያለው መረጃ ተደራሽ ማድረግ መቻሉን ወ/ሮ ሲፈን ባዩ አንስተዋል። የምናስተላልፋቸው መልዕክቶችም የህዝቡን የልማት ተሳትፎ የሚያጎለብቱ እና በመንግስትና በህዝብ መካከል ያለው የልማት ትስስር እንዲጠናከር የሚያደርጉ ሊሆን ይገባል ብለው የመረጃና የኮሙኒኬሽን ስራዎቻችን ለሃገርና ለትውልድ ግንባታ ለማዋል የዘርፉ አመራር፣ባለሙያዎችና ማህበረሰብ አንቂዎች ተግተው መስራት አለባቸው በማለት ወ/ሮ ሲፈን አክለው ገልፀዋል። በበጀት አመቱ በጽ/ቤቱ የተከናወኑ ተግባሮች እንዲሻሻሉ የሚደረገው ድጋፍና ክትትል ተጠናክሮ መቀጠል አለበት በማለት በቀጣይ የተሻለ የመረጃ ልውውጥ በማድረግ ቀልጣፍ የሆነ የመረጃ ተደራሽነት እንዲኖር ተግባራትን በቅንጅት መሠራት ይገባል ሲሉ አንስተዋል። ጽ/ቤቱ በ 2017 ዓ.ም ያከናወናቸው የኮሙኒኬሽን ስራዎች የሚበረታቱ ናቸው ብለው እኛ በቅንጅት መስራታችን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል። ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የ ልደታ ክ/ከተማ ኮሚንኬሽን ገፆችን ይከታተሉ !! http://linktr.ee/lidetacommunication1

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች