image
image
image
image
image

የክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት እየሰራ ያለውን ዘመኑን የዋጀ የኮሙኒኬሽን ስራዎች እና የዲጂታል ሚድያ ተግባራትን ለየካ አቻው ልምዱን አካፈለ።

ታህሳስ 7, 2018
የልደታ ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት እየሰራ ያለውን ዘመኑን የዋጀ የኮሙኒኬሽን ስራዎች እና የዲጂታል ሚድያ ተግባራትን ለየካ አቻው ልምዱን አካፍሏል። በእለቱም በክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት እየተሰሩ ያሉና ለሌላው ተሞክሮ ይሆናሉ የተባሉ ስራዎችን አስመልክቶ ገለፃ ተደርጓል። የክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሲፈን ባዩ ወቅታዊ ስራዎችን ማዕከል ያደረገ የህዝብ ግንኙነት፣ የዲጂታል ሚዲያና የፕሮዳክሽን ቡድኖች በቅንጅት በመስራት የህትመት፣ የዜናና የቪዲዮ ፕሮዳክሽን ስራዎች በሚፈለገው የጥራት ደረጃ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። በክከተማው የመረጃ ስርዓትን ዘመናዊ ፣ፈጣንና ተደራሽ ለማድረግ ተጨባጭ ስራ መሰራቱን የጠቆሙት ወ/ሮ ሲፈን የልደታ ፋና ፕሮግራም፣ የቅኝትና የእለታዊ ዜናዎች እንዲሁም የህትመት ስራዎችና ዲጂታል ሚድያ ዙሪያ ሰፊ የማስተዋወቅ ስራ ተሰርቷል ብለዋል። የልምድ ልውውጡ አዳዲስ የፈጠራ ስራዎችን በመቅሰም በመንግስትና በህዝብ መካከል የድልድይ ሚናችንን በአግባቡ እንድንወጣ ያግዘናል ያሉት የየካ ክ/ከተማ ኮሚንኬሽን ባለሞያዎች ወደተቀራራቢ አፈፃፀም በመምጣት የጋራ ተልእኮአችንን ለማሳካት በቅንጅት እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል ። በመጨረሻም የመረጃ ማዕከልን የጎበኙ ሲሆን የመረጃ አደረጃጀት፣ አያያዝንና የአሰራር ስርዓትን አስመልክቶ የተሰሩ ስራዎችን አይተዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች