በብልጽግና ፓርቲ የሴት ክንፍ አባላት በሁለተኛው መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎች እና የቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ውይይት አካሄደ።
ለውይይቱ መነሻ የሚሆን ሰነድ በልደታ ክፍለ ከተማ ሴቶች ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ሀላፊ ቀርቧል
የብልጽግና ፓርቲ በሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ባሳለፍቸው ውሳኔዎች ባስቀመጣቸው አቅጣጫዎች የብልፅግና ፓርቲ ሴት ክንፍ አባላትና ደጋፊዎች ሚናቸው ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ።
የልደታ ክፍለ ከተማ ም/ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ነፃነት ደረሰ በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ባስተለፉት መልዕክት በብልጽግና ፓርቲ የጉባኤ ውሳኔው አቅጣጫ ላይ የሴቶች ሚና ምን ይመስላል የሚለው በግልፅ በመወያየት ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል በማለት በሴቶች ተጠቃሚነት ላይ ሰፊ ስራ ሲሰራ የነበረ ሲሆን ይህን ለማስቀጠል በሚቻል መልኩ የሴቷን ውስብስብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል መልኩ ፕሮጀክቶችን በመንደፍ ሴቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ ተችሏል በማለት ገልፀዋል።
ወ/ሮ ነፃነት አያይዘው ፓርቲያችን ሰው ተኮር ነው ስንል የሰራነው እያንዳንዱ ተግባር ለሴቶች ሁለንተናዊ ብለፅግን በሚያረጋግጥ መልኩ እየተሰራ ሲሆን ከዚህ የበለጠ እንዲሆን በዛሬው ውይይት የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ሁሉም ሚናውን ሊወጣ ይገባል በማለት ገልፀዋል።
የልደታ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ሀላፊና የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ደረጀ ዲሪብሳ ሴቶች ፓርቲው ያስቀመጠውን አቅጣጫ ተግባራዊ በማድረግ፤ልማትና ሰላምን በማስፈን ረገድ የማይተካ ሚና እንዳላቸው በመግለፅ የብልጽግና ጉዞ ለማፋጠን የሴቶች ሚና ከፍተኛ ነው በማለት ገልፀዋል።
የልደታ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሰናይት ሞሲሳ በበኩላቸው የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ አባላት በጉባኤው የተቀመጠውን አቅጣጫና ተልዕኮ ተገንዝቦ በብቃት የመፈጸም ሁሉንም ሴቶች ለጋራ አላማ በመሰለፍ ሚናቸውን መወጣት አለባቸው በማለት ገልፀው የሴት ክንፋ ያነገባቸው አላማዎች በኢኮኖሚያዊና በማህበራዊ ብልፅግና ጉዞ ለማሳካት ሚናችሁን ልትወጡ ይገባል በማለት ገልፀዋል።
ተሳታፊውም የቀረሰው ሰነድ የተሻለ ነው በማለት የፓርቲውን ውሳኔና አቅጣጫ በመተግበር ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ሲሉ አንስተዋል።
ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የ ልደታ ክ/ከተማ ኮሚንኬሽን ገፆችን ይከታተሉ !!
http://linktr.ee/lidetacommunication1