አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን የከፍታችን ማሳያ ነው ሲል የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ገለፀ
በልደታ ክ/ከተማ ነዋሪ የሆኑ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከልን ጎብኝተዋል።
የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ እንደተናገሩት አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ኢትዮጲያን ከዓለም ጋር የሚያስተሳስር ነው ብለው ኢትዮጲያን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የማድረጉ ተግባር በሁሉም ዘርፍ ተጠናክሮ ይቀጥላልም ሲሉ ገልፀዋል።
በኢኮኖሚው ዘርፍ የኢትዮጲያ ከፍታ ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና አለው ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ሁሌም ቢሆን ኢትዮጲያን ከዓለም ጋር ለማቆራኘት ለሚሰሩ የለውጥ መሪዎቻችን ምስጋና ይገባል በማለት ገልፀዋል።
ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አክለውም አዲስ አበባን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ከተማ ለማድረግ መንግስት በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀው የሚሰሩ እጆች ሁሌም የለውጥ አብነቶች ስለሆኑ ሁሉም ዜጋ የመሪዎቹን ፈለግ ተከትሎ ሌት ከቀን በመስራት ለውጥ ማስመዝገብ አለበት ብለዋል።
የጉብኝቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የለውጡ መንግስት የማይሳኩ የሚመስሉ ትላልቅ ፕሮጀክቶችን በተግባር አሳክቶ አሳይቶናል ብለው በዛሬው ጉብኝትና በተመለከቱት ስራ መደሰታቸውንም ገልፀዋል።
ለዶ/ር ዓብይ አህመድ እና ለከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ምስጋና አቅርበዋል።
ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የ ልደታ ክ/ከተማ ኮሚንኬሽን ገፆችን ይከታተሉ !!
http://linktr.ee/lidetacommunication1