የተቋሙ ስልጣን ፤ ተግባርና ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮች
በጽ/ቤት ውስጥ ያሉ የኮሚዩኒኬሽን ቡድኖች በክፍለ ከተማ መንግሥት ሠራተኞች ሕግ መሠረት በሜሪት እንዲመደቡ ያደርጋል፤ አፈፃፀሙንም ይከታተላል፤
የማህበራዊ ገጾችን የዕለት ተዕለት ዘገባ ቅኝት እና መረጃዎችን በመሰብሰብ ይተነትናል ለሚመለከታቸው አካላት ያሠራጫል፤
የሚዲያ መሰረተ ልማት የሚጠናከርበትን፣ የሚስፋፋበትን ፣ በተገቢው ቴክኖሎጂና ብቃት ባለው የሰለጠነ ባለሙያ የሚደራጅበትን ሥርዓት ይቀይሳል፤
ሥራና ሠራተኛ ለሚያገናኙ ኤጀንሲዎች የብቃት ማረጋገጫ በህግ መሰረት ይሰጣል፤ ድጋፍ ያደርጋል፤ መሥራታቸውን ያረጋግጣል፤ ይሰርዛል፤
ሥራና ሠራተኛ ለሚያገናኙ ኤጀንሲዎች እና የግል የስራ ሁኔታ ቁጥጥር አገልግሎት አቅራቢዎች የብቃት ማረጋገጫ መስጠት፤
ስለውጭ አገር ሥራ ስምሪት እና ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር የግንዛቤ ማሳደጊያ ሥራዎችን መስራት፤