image
image
image
image
image

የክፍለ ከተማው አስተዳደር ካቤኔ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሔደ።

ጥቅምት 16, 2018
የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በልማት እና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ባላቸው አጀንዳዎች ዙሪያ ተወያይቶ የውሳኔ ሀሳቦችን አሳርፏል። የካቢኔ አባላቱ በክ/ከተማው እየተሰሩ የሚገኙትን ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን ፕሮጀክቶቹ የደረሱበትን አፈፃፀሞች በመገምገም ውሳኔ ሰጥተውባቸዋል። በክፍለ ከተማው ነዋሪውን በልማት ተጠቃሚ የሚያደርግ፤ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የሚፈቱ ሌሎች መሰረተ ልማቶች እና ፕሮጀክት ግንባታዎች ስታንዳርድ በጠበቀና በተቀናጀ መልኩ መፈፀም እንደሚገባ ተገልጿል። የልማትና የመልካም አስተዳደር እንዲሁም ልዩ ልዩ ፕሮጀክት ግንባታ አጀንዳዎች ላይ ተወያይተን የወሰናቸውን ጉዳዮች በጠንካራ ክትትልና ድጋፍ መፈጸም ከሁሉም አስፈጻሚ አካላት እንደሚጠበቅ ተመላክቷል። የካቢኔ አባላቱ እንደገለፁት የህዝባችንን ተጠቃሚነትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ምላሽ መስጠት የትኩረት ማዕከል አድርገን እየሰራን እንገኛለን ብለው የተቀመጠው የውሳኔ ሃሳብ ተግባራዊ ለማደረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች