• የልደታ አስተዳደር ህንፃ 2ኛ ወለል ቢሮ ቁጥር 205
  • +251912689710
  • ዓርብ, ህዳር 14, 2016 ዓ.ም

image
image
image
image
image

በአለም አቀፍ ለ114ኛ በኢትዮጵያ ለ49ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘው የሴቶች ቀን "ፈጣን እና ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል " በሚል የሴቶችና ህፃናት ማ /ጉ/ ፅ/ ቤት ከጤና ጋር በመተባበር የማህፀን በር እና ጡት ጫፍ ካንሰር ምርመራ እና ደም ልገሳ ተደረገ።

የካቲት 27, 2017
የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ ባስተላለፉት መልዕክት ሴቶችን በሁሉም ዘርፍ ማሳተፍ አስፈላጊነትና ጠቀሜውም እንደ ሀገር የጎላ ነው በማለት በአገር አቀፍና በአለም ደረጃ የሴቶች ተጽእኖ ፈጣሪነት እያየለ መምጣቱን በመግለፅ ይህን ልምድ በማሳደግ ሴቶችን አሁን ካለውም በላይ በሁሉም ዘርፍ ተሳታፊነታቸው ማሳደግ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡ የልደታ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ምክትል ሀላፊና የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ደረጄ ድሪባ እንደገለፁት ሴቶች ከወንዶች እኩል ተሳትፎ ማድረግ ይገባታል በማለት ሴት እናቶቻችን እህቶቻችን እንዲሁም ልጆቻችን ላይ የሚደርሰውን ማግለል በማቆም በሁሉም ዘርፍ ሴቶችን በማሳተፍ ውጤታማ መሆን ተችሏል። የልደታ ክፍለ ከተማ ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳዮች ጽ/ጉዳይ ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ሄለን መሀመድ እንደገለፁት የሴቶች ጤና በመጠበቅና ሴቶችን በኢኮኖሚ በማብቃት ፣ የሴቶችን በፖለቲካ ተሳትፎ በማሳደግና የሴቶች መብት በማረጋገጥ ረገድ የተሰራ ስራ የተሻለ ነው በማለት በቀጣይም ይህን አጠናክረን ማቀጠል ይጠበቅብናል በማለት ገልፀዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አህመድ እንድሪስ ባስተላለፉት መልዕክት ማንኛውም ሴት ይህ አስከፊ በሽታ ሲደርስባት ሳይሆን ቅድመ ምርመራ በማድረግ ራሷን በማወቅ ይገባታል በማለት ለሴቶች ትኩረት ሰጥቶ መስራት ለሃገር መስራት መሆኑን ገልፀው የጤና ባለሙያዎች የሚያደርጉትን የስራ ጥረቶች ምስገና አቅርበው።ይህ ምርመራ በነፃ በመምጣቱ ዛሬ የመጣችሁ ሴቶችና ሌሎች ሴቶች ቅድመ ምርመራ በማድረግ ከበሽታው ራሳቸውን እንዲጠብቁ ጥሪ አስተላልፈዋል።