image
image
image
image
image

"የሴቶች ድምጽ ለዕኩልነት እና ለበለፀገች ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል የ130ኛው የአደዋ ድል በዓል ፓናል ዉይይት ተካሄደ

የካቲት 10/6/2018, 2018
የልደታ ክፍለ ከተማ ሴቶችና ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ ቤት "የሴቶች ድምጽ ለዕኩልነት እና ለበለፀገች ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል ከክፍለ ከተማው የሴት አደረጃጀቶች ጋር የፓናል ዉይይት አካሄደ። በመድረኩ ተገኝተዉ ንግግር ያደረጉት የልደታ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ምክትልና ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊና አቶ አሰፋ ቶላ ባስተላለፉት መልዕክት ይህ የድል በዓል ሴቶች በቆራጥነት ከተነሱ የማይቻለውን ማድረግ እንደሚችሉ ማሳያ ነዉ ብለዋል። ወቅት ሀገራዊ ሰላምን ለማረጋገጥና የኢኮኖሚ እድገትን ለማፋጠን የሴቶች አደረጃጀቶች ሚና ከመቼውም ጊዜ በላይ ወሳኝ መሆኑን የገለፁት አቶ አሰፋ አያይዘው ከአድዋ የተገኘውን የአንድነትና የፅናት መንፈስ ወደ ልማት በመቀየር ሴቶች በከተማ ግብርና፣ በኢንተርፕራይዝ እና በማህበራዊ ዘርፎች በንቃት ሊሳተፉ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል። ​በመድረኩ ላይ ተገኝተዉ መልዕክት ያስተላለፉት የክፍለ ከተማዉ ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሄለን መሀመድ እንደገለፁት፤ የዘንድሮው የ130ኛው የአደዋ ድል በዓል ከመጋቢት 8 ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን እየተከበረ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በዓሉን "ድርብ በዓል" እንደሚያደርገው ገልፀዉ የአደዋ ድል የጥቁር ህዝቦች ኩራት ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ሴቶች በጀግንነት የተሳተፉበትና የላቀ የድል ታሪክ የሰሩበት መሆኑን ኃላፊዋ አስታውሰዋል። አቶ ጀንበሩ የክፍለ ከተማዉ ምክትል ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ በፓናል ዉይይቱ ፣''የአደዋ ድልና የሴቶች ሚና በሚል ርዕስ'' ሰነድ አቅርበዉ ዉይይት ተደርጓል። ተሳታፊዎችም የአደዋን የድል መንፈስ በመሰነቅ ለሀገር ብልጽግና እና ለሰላም ግንባታ ያላቸውን ዝግጁነት አረጋግጠዋል። ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የ ልደታ ክ/ከተማ ኮሚንኬሽን ገፆችን ይከታተሉ !! http://linktr.ee/lidetacommunication1

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች