የልደታ ክፍለ ከተማ "ትናንት፣ ዛሬና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና"በሚል ቃል ለነዋሪዎች ነፃ የህክምና አገልግሎት ተሰጠ
የልደታ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ከህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን የነፃ ህክምና መርሃ ግብር አካሄደ
የልደታ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ደረጄ ድሪብሳ በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት ከመጋቢት ትሩፋት ውስጥ አንዱ የሆነው የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን በማሻሻልና ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠር በትኩረት እየሰራን እንገኛለን በማለት ነፃ የህክምና አገልግሎት በመስጠት ፣በጤና ተቋማት በርካታ ስራዎች በመስራት ጤናማ ዜጋ በመፍጠርና ቀልጣፋ አገልግሎትን በመስጠት ረገድ እየተሰራ ያለውን አጠናክረን መስራት ይገባል ብለዋል።
የልደታ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አህመድ እንድሪስ እንደተናገሩት አብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል ነፃ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ ጤናቸው የተጠበቀ እንዲሆን ነፃ የህክምና መርሃ ግብር በማዘጋጀት የዜጎቻችንን ጤና የመጠበቅ ተግባር እያከናወንን ነው ከዚህ የተሻለ አገልግሎት የሚያስፈልጋቸው ካሉ ፣ ከሆስፒታሎች ጋር በመተባበር ነፃ የህክምና አገልግሎት እንደሚያገኙ ይደረጋል ሲሉ ገልፀዋል።
የልደታ ክፍለ ከተማ የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ እንግዳው ጓዴ እንደገለጹልን፤ ለማህበረሰብ የነፃ ህክምና አገልግሎት በመስጠት ጤናማ ህዝብ ለመፍጠር ያለው አበርክቶ የተሻለ መሆኑን የገለፀው በተለይ ህክምናው ብዝዎችን በሽታውን አስቀድመው መከላከል እንዲችሉ ግንዛቤ ከመፍጠር ባለፈ መታከም ለማይችሉ የማህበረሰብ ክፍሎችም ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።