image
image
image
image
image

በአድዋ ድል መንፈስ ህዝባችንን በቁርጠኝነት ለማገልገል ከምንጊዜው በላይ ዝግጁ ነን":- የልደታ ክ/ከተማ የመንግስት ሠራተኞች

የካቲት 8/6/2018, 2018
በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር "የአድዋ አደራ፣ አንድነት ለሉዓላዊነትና ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የ130ኛውን የአድዋ ድል በዓልን ምክንያት በማድረግ ከመንግስት ሠራተኞ ጋር የውይይት መድረክ ተካሄደ። ​የውይይት መድረኩን የመሩት የክ/ከተማው ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ዘሪሁን ሺፈርዳ ሲሆኑ፣ የአድዋ ድል የኢትዮጵያውያን የነፃነትና የብሔራዊ ክብር መገለጫ መሆኑን ገልጸዋል። ድሉ ለዛሬው ሀገራዊ ግንባታና ለነገው ብሔራዊ ከፍታ እንደ መነሻ ሊያገለግል እንደሚገባም የተከበሩ አቶ ዘሪሁን በአጽንኦት ተናግረዋል። የተከበሩ ዋና አፈ-ጉባኤው ከአድዋ ድል በዓል የአሁኑ ትውልድ ድህነትን ታሪክ በማድረግ ዘለቄታ ያለው ኢኮኖሚያዊ ብልፅግናን ከማረጋገጥ ባሻገር አዲሱ ትውልድ ከግጭት ወደ ውይይት፣ ከመከፋፈል ወደ ትብብር በመቀየር፤ ለነገ የታሪክ አሻራ ማኖር እንደሚገባ አሳስበዋል። በመድረኩ ላይ የውይይት ሰነዱን ያቀረቡት የክ/ከተማው ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ መቅደስ ያደታ በበኩላቸው የአንድ ሀገር ብሔራዊ ጥቅም ሊረጋገጥ የሚችለው የሀገሪቱ ሕልውና እና ሉዓላዊነት ሲከበር መሆኑ አንስተዋል። ​ወ/ሮ መቅደስ አክለው አሁን ያለንበት ወቅት በዓድዋ መንፈስ ፈተናዎችን አሸንፈን ታላቅነታችንን ዳግም የምናረጋግጥበትና የማንሰራራት ዘመን ሊሆን እንደሚገባ ገልፀው የመንግስት ሠራተኛው በአድዋ ድል መንፈስ ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ቅንነት የተሞላበት አገልግሎት እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል። ​የአድዋ ድል ኢትዮጵያውያን በብሔር፣ በቋንቋና በሃይማኖት ሳይከፋፈሉ በአንድ ጥላ ሥር በመሰባሰብ ጠንካራ ብሔራዊ አንድነትን የፈጠሩበትና የአሸናፊነት ሥነ-ልቦናን ያላበሰ ታሪካዊ ድል መሆኑን ያነሱት ደግሞ የክ/ከተማው መንግስት ሠራተኞች ናቸው። አያቶቻችን ለሀገራችን ሉዓላዊነት የከፈሉትን መስዋዕትነት እየዘከርን እኛም በአድዋ ድል መንፈስ ህዝባችንን በቁርጠኝነት ለማገልገል ከምንጊዜው በላይ ዝግጁ ነን ሲሉ የመንግስት ሠራተኞቹ በመድረኩ ቃል ገብተዋል። ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የ ልደታ ክ/ከተማ ኮሚንኬሽን ገፆችን ይከታተሉ !! http://linktr.ee/lidetacommunication1

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች