• የልደታ አስተዳደር ህንፃ 2ኛ ወለል ቢሮ ቁጥር 205
  • +251912689710
  • ዓርብ, ህዳር 14, 2016 ዓ.ም

image
image
image
image
image

የልደታ ክፍለ ከተማ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ጽ/ቤት የኪነ ጥበብ ምሽት "መግባባትና አብሮነት ለጋራ ህልማችን ስኬት" በሚል መሪ ቃል የልደታ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ገዢ ትርክትን ለማስረፅ ፕሮግራም አካሄደ።

የካቲት 27, 2017
በመርሃግብሩ ላይ የተለያዩ አገራዊ አንድነትን የሚዘክሩ ዘፈኖች፣ ውዝዋዜዎች፣ ስነ ግጥሞችና ሌሎች የኪነ ጥበብ ትዕይንቶች ታይተዋል። በኪነ ጥበብ ምሽቱ ላይ የልደታ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሃፍቱ ብርሃኑ፣ የልደታ ክፍለ ከተማ ም/ዋና ሰራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ነፃነት ደረሰ ፣ የክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ም/ሀላፊና የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ደሰጄ ድሪብሳ የክፍለ ከተማ አመራሮችና የወረዳ አመራሮች በትዕይንቱ ላይ ተገኝተዋል። የሀገራችንን ከፍታ በማሳየትና ህብረ ብሔራዊ አንድነት የበለጠ በማጉላት ለጋራ አንድነታችን በጋራ ለመቆም ገዢ ትርክትን ማስረፅ ከሁላችንም ይጠበቃል ። ኪነ -ጥበብ ለሀገር አንድነትና መግባባት እንዲሁም ለጀመርነዉ የብልፅግና ጉዞ ትልቅ መሳሪያና አቅምም ጭምር ነዉ" በአሁን ሰአት እንደ ሀገር ተስፍችን ብሩህ እንዲሆን በልማትና እድገት ጉዞ ላይ እንድናተኩር ከመቼዉም በተሻለ ወቅት ላይ እንገኛለን። በዚህ ጊዜም ኪነጥበብ የሚጫወተዉ ሚና ከፍተኛ ነዉ ። ሀገርን በሁሉም አጀንዳ በአንድነት ለማሰለፍ ኪነጥበብ ትልቅ አርማና መሳሪያ ነው። ሀገር ለዜጎቿ ምቹ ሰላማዊና እድገት ያላት ሆና እንድትቀጥል ብዙ ባለድርሻ አካላት ቢኖሩም እንኳን ኪነጥበብ ያላትን ሚና ግን ማንም ሊመጣዉ አይችልም። ሀገርን በሰዎች ልቦና ዉስጥ በደንብ ቀርጾ አእምሮን፣ እጆችንና እግሮችን በሙሉ አቅም ለሀገር ለማዘጋጀት ኪነጥበብ ያላት ድርሻ ጉልህ ነዉ። " በሀገሪቱ እየታየ ያለውን የሰላም፣ የመቻቻልና የህብረ ብሄራዊነት እሴት በኪነጥበብ ጎልቶ እንዲወጣ ማስቻል አላማ አድርጎ የተዘጋጀ የኪነጥበብ ምሽት እንደሆነም ተገልፃል።