image
image
image
image
image

የአድዋ አደራ" በሚል መሪ ሀሳብ 130ኛው የአድዋ ድል በዓል አከባበርን አስመልክቶ ከወጣቶች ጋር ውይይት ተካሄደ።

የካቲት 7/6/2018, 2018
የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር "የአድዋ አደራ፣ አንድነት ለሉዓላዊነትና ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የ130ኛውን የአድዋ ድል በዓልን ምክንያት በማድረግ ከወጣቶች ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ። ​የውይይት መድረኩን በንግግር ከፍተው ውይይቱን ያካሄዱት የክ/ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ አሰፋ ቶላ ሲሆኑ፣ የአድዋ ድል የኢትዮጵያውያን የነፃነትና የብሔራዊ ክብር መገለጫ መሆኑን ገልጸዋል። አቶ አሰፋ፤ ድሉ ለዛሬው ሀገራዊ ግንባታና ለነገው ብሔራዊ ከፍታ እንደ መነሻ ሊያገለግል እንደሚገባም በአጽንኦት ተናግረዋል። ከአድዋ ድል በዓል የአሁኑ ትውልድ ድህነትን ታሪክ በማድረግ ዘለቄታ ያለው ኢኮኖሚያዊ ብልፅግናን ከማረጋገጥ ባሻገር አዲሱ ትውልድ ከግጭት ወደ ውይይት፣ ከመከፋፈል ወደ ትብብር በመቀየር፤ ለነገ የታሪክ አሻራ ማኖር እንደሚገባ ኃላፊው አሳስበዋል። የክ/ከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንተነህ በፍቃዱ በበኩላቸው የአንድ ሀገር ብሔራዊ ጥቅም ሊረጋገጥ የሚችለው የሀገሪቱ ሕልውና እና ሉዓላዊነት ሲከበር መሆኑ አንስተዋል። ​አቶ አንተነህ አክለው አሁን ያለንበት ወቅት በዓድዋ መንፈስ ፈተናዎችን አሸንፈን ታላቅነታችንን ዳግም የምናረጋግጥበት የማንሰራራት ዘመን ሊሆን እንደሚገባ ገልፀዋል። ​በመድረኩ ላይ የውይይት ሰነዱን ያቀረቡት የልደታ ክ/ከተማ የብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ ጀምበሩ ኢርኮ ባቀረቡት ሰነድ ላይ የአድዋ ድል ኢትዮጵያውያን በብሔር፣ በቋንቋና በሃይማኖት ሳይከፋፈሉ በአንድ ጥላ ሥር በመሰባሰብ ጠንካራ ብሔራዊ አንድነትን የፈጠሩበትና የአሸናፊነት ሥነ-ልቦናን ያላበሰ ታሪካዊ ድል መሆኑን አብራርተዋል። ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የ ልደታ ክ/ከተማ ኮሚንኬሽን ገፆችን ይከታተሉ !! http://linktr.ee/lidetacommunication1

መልዕክትዎን ይላኩ