image
image
image
image
image

አስተዳደሩ የአገልግሎት ቀንን ምክንያት በማድረግ የተቀናጀ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

ጥር 27/2018, 2018
የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የነዋሪዎችን መሠረታዊ ጥያቄዎች ለመመለስ ዕረቡና አርብን ሙሉ ቀን በመጠቀም ቀልጣፋና ፍትሃዊ እንዲሁም ግልፀኝነት የሰፈነበት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ በተቀናጀ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ፣ እንዲሁም ሌሎች የተቋም ሀላፊዎች ተገልጋዮችን እያስተናገዱ መሆኑን መመልከት ተችሏል። አስተዳደሩ በተቀናጀ አገልግሎት ለነዋሪዎች ጥያቄ ፈጣን ምላሽ በመስጠት ግልፀኝነትን እና ብልሹ አሰራር በማስቀረት የተገልጋይ እርካታን የሚያረጋግጥ በመሆኑ በልዩ ትኩረት በመስራት ላይ ነው። እየተሰጠ ባለው የተቀናጀ አገልግሎት፤ ተገልጋዮች ደስተኞች ሆነው ሲያመሰግኑ የልደታ ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን በቦታው ተገኝቶ ተመልክቷል።

መልዕክትዎን ይላኩ