በልደታ ክፍለ ከተማ የ75 ቀናት የስራ ዕድል ፈጠራ እና የሌማት ቱሩፋት ስራ ተገመገመ።
የልደታ ክፍለ ከተማ ም/ዋና ስራ አስፈጻሚና ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ነጻነት ደረሰ እንደተናገሩት መንግስት የስራ ዕድል ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በትኩረት በመስራቱ የስራ ዕድል ፈላጊ ወጣቶችና ሴቶች ወደ ስራ ማስገባት የተቻለ መሆኑን ገልጸው በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ላይ በአፈጻጸማችን ግባችንን እንድንመታና ስራ ፈላጊዎችን በሚፈለገው ልክ ወደ ስራ ለማስገባት የቀሩትን ስራዎች በመገምገም ክፍተቶችን ማስተካከል ይገባናል ብለዋል።
ወ/ሮ ነጻነት አክለውም የዜጎችን የስራ ዕድል ተጠቃሚነት በማረጋገጡ በኩል የስራ ዕድል ለሚፈጠርላቸው አካላት የተለያዩ የስልጠና ተቋማት ጋር በመተባበር ወደ ስራ ሲገቡ ውጤታማ መሆን የሚችሉበትን መንገድ ግንዛቤ አግኝተው ወደ ስራ እንዲገቡ ማድረጋቸውን ገልጸው የመንግስትና የግል ተቋማት እንዲሁም ባለሃብቶች የስራ ዕድል ፈላጊዎችን በማብቃቱ በኩል የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ ሊያሳድጉ ይገባል ብለዋል።
የሌማት ቱሩፋት ስራን በማጠናከር ዜጎች የምግብ ዋስትናቸውን እንዲያረጋግጡ ማድረግ ተችሏል ያሉት ወ/ሮ ነፃነት በቀጣይም የሌማት ቱሩፋት ስራን የበለጠ በማላቅ ዜጎች በምግብ ራሳቸውን እንዲችሉ የማድረግ ተግባር ይከናወናል ሲሉ ገልፀዋል።
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ተስፋነሽ ጋሻው እንደተናገሩት የሌማት ቱሩፋት ተግባራችን በትኩረት በመሰራቱ ውጤት አምጥቷል ብለው አሁን ላይ በርካታ ዜጎች ይህንን ተግባር እየሰሩ በምግብ እራሳቸውን እየቻሉ ይገኛል በማለት ገልፀዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች እንደተናገሩት የስራ ዕድል ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ ሁሉም ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ ገልጸው ያሉንን ሀብቶች በመጠቀም የተያዘውን የስራ ዕድል ፈጠራ ዕቅድ ውጤታማ ማድረግ ይገባል ብለዋል።