በልደታ ክፍለ ከተማ Measles and VAS= 23915
Deworming= 18972 ለሚሆኑ ህጻናት ክትባት መስጠት ሊጀመር እንደሆነ የክፍለከተማው ጤና ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
ፅህፈት ቤቱ በሰጠን መረጃ ክትባቱ በከተማ ደረጃ ከ600 ሺ በላይ እንደ ክፍለከተማ ደግሞ Measles and VAS= 23915
Deworming= 18972 ህፃናት የተቀናጀ የኩፍኝ መከላከያ ክትባት እንደሚሰጥ ገልፁዋል፡፡
ይህ የክትባት ዘመቻም ከግንቦት 18/2017 ለተከታታይ 10 ቀናት እንደሚሰጥ የፅህፈት ቤቱ ሀላፊ አቶ አህመድ እንድሪስ ገልፀዋል፡፡
ክትባቱም በመንግስትም በግልም የህፃናት ማቆያ፣ በትምህርት ቤቶች ጊዚያዊ ጣቢያዎች ላይ ይሰጣልም ተብሏል፡፡
በመደበኛ ክትባት ያልጀመሩ፣ ክትባቱን አቋርጠው እቤት ላሉ ህፃናት፣ ለነፍሰጡርና ለሚያጠቡ እናቶች የስርአተ ምግብ ልየታ እንደዚሁም የቫይታሚን ኤ ጠብታና የአንጀት ትላትል መከላከያ ኪኒን የመስጠት፣ የታመሙ ህፃናት በመለየት ወደ ጤና ተቋም መላክ ስራ ከክትባቱ ጎን ለጎን ይሰራለም ብለዋል፡፡
ወላጆችም ይህን በመገንዘብ በተጠቀሰው ቀን ከ9 ወር እስከ 5 አመት የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ህፃናትን ለክትባት እንደዚሁም ጎን ለጎን ለሚሰሩ ስራዎችም ተባባሪ እንዲሆኑ ፅህፈት ቤቱ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡