• የልደታ አስተዳደር ህንፃ 2ኛ ወለል ቢሮ ቁጥር 205
  • +251912689710
  • ዓርብ, ህዳር 14, 2016 ዓ.ም

image
image
image
image
image

"ትናንት፣ ዛሬና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና "!! በልደታ ክ/ከተማ የመጋቢት 24 ፍሬዎች የሆኑ ማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ፕሮጀክቶች ተመረቁ

መጋቢት 24, 2017
በክ/ከተማው "ትናንት ፣ዛሬና ነገን ለኢትዮጲያ ልዕልና" በሚል መሪ ቃል እየተዘከረ የሚገኘውን መጋቢት 24 ምክንያት በማድረግ ፕሮጀክቶች ተመርቀዋል። የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ ባደረጉት ንግግር መጋቢት 24 የሀገራችን ብልፅግና መሰረት የተጣለበት ከድህነት እና ኃላቀርነት ለመውጣት የሚያስችሉ ተግባራት መከናወን የጀመሩበት ነው ብለው በመጋቢት 24 የፕሮጀክቶች አፈፃፀም ከመጓተት ወጥቶ ፕሮጀክቶችን በአጠረ ጊዜ የመፈፀም ባህል የዳበረበት ነውም ሲሉ ገልፀዋል። የለውጡ መንግስት በርካታ የመጋቢት ፍሬዎችን እውን አድርጓል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ በተለይም የሀገር ኩራትና ቅርስ የሆነውን የታላቁ ህዳሴ ግንድብ ግንባታ ከቆመበት አንስቶ አሁን ያለበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ በማድረግ እና የትምህርት ቤት ምገባን በማስጀመር ረገድ ውጤታማ ስራ አከናውኗል ሲሉ ተናግረዋል። ፕሮጀክቶች በአጠረ ጊዜ በጥራት እንዲጠናቀቁ 24/7 ሲሰሩ ለነበሩ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል ዋና ስራ አስፈፃሚዋ። የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ አማካሪ የሆኑት አቶ ጥላሁን ፈቃዱ በበኩላቸው መጋቢት 24 በጠንካራ የስራ ባህል ድህነትን ታሪክ ማድረግ የጀመርንበት እንዲሁም ትውልድን የሚያንፁ ፕሮጀክቶች እውን መሆን የቻሉበት ነው ብለዋል። ፕሮጀክቶችን መጀመር ብቻ ሳይሆን በጥራትና በፍጥነት መጨረስ ባህል እንዲሆን መሰረት የተጣለበት ነው ያሉት አማካሪው በቀጣይ በርካታ ትውልድ የሚያፈሩ ህንፃዎችን ገንብተን የሀገራችንን ብልፅግና እያረጋገጥን እንቀጥላለን ሲሉ ገልፀዋል። የልደታ ክ/ከተማ የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ናርዶስ መንክር እንደተናገሩት አስተዳደሩ በተቋማት ያሉ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት በጀት መድቦ ፕሮጀክቶችን እየገነባ ይገኛል ብለው በዛሬው እለትም የመጋቢት ፍሬ የሆኑ ማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን በአጠረ ጊዜ በጥራት ገንብተን አጠናቀናል ሲሉ ተናግረዋል። በቀጣይ የተጀመሩ ፕሮጀክቶች አሉን እነዚህን ፕሮጀክቶች በአጠረ ጊዜ አጠናቀን አገልግሎት እናስጀምራለን ብለዋል አቶ ናርዶስ።