• የልደታ አስተዳደር ህንፃ 2ኛ ወለል ቢሮ ቁጥር 205
  • +251912689710
  • ዓርብ, ህዳር 14, 2016 ዓ.ም

image
image
image
image
image

የልደታ ክ/ከተማ "ንፁህ ወንዞች ፤ለጤናማ ህይወት"በሚል መሪ ቃል የወንዝ ዳርቻ ልማትና ብክለት መከላከል ደንብ ቁጥር 180/2017 ዙሪያ ለአመራሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ

መጋቢት 2, 2017
"የወንዝ ዳርቻዎችን በማልማት እና ከብክለት በመከላከል ውብ ፅዱ እና ለኑሮ ተስማሚ አካባቢን እውን ማድረግ ይኖርብናል" ወ/ሮ አበባ እሸቴ "የከተማችን ወንዞች ተጨማሪ የውበት ነፀብራቅ እንጂ የጤና ጠንቅ ሊሆኑ አይገባም" አቶ ሃፍቱ ብርሀኑ የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር "ንፁህ ወንዞች ፤ለጤናማ ህይወት"በሚል መሪ ቃል የወንዝ ዳርቻ ልማትና ብክለት መከላከል ደንብ ቁጥር 180/2017 ዙሪያ ለአመራሩ የንቅናቄ ማስጀመሪያና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል። የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ በመድረኩ ባስተላለፍት መልዕክት የወንዝ ዳርቻዎችን በማልማት እና ከብክለት በመከላከል ውብ ፅዱና ለኑሮ ተስማሚ አካባቢን መፍጠር ይገባል ብለው የወንዝ ዳርቻዎችን ከብክለት መከላከልና ወንዞችን ማልማት የሁሉም ዜጋና የተቋማት ኃላፊነት ሊሆን ይገባል ሲሉ ተናግረዋል። ከተማችንን የበለጠ ውብ ፅዱና አረንጓዴ ለማድረግ የወንዝ ዳርቻ ልማት ወሳኝነት አለው ያሉት ወ/ሮ አበባ ወንዞችን ከብክለት መከላከል እና የወንዝ ዳርጃዎችን ማልማት ትኩረት ተሰጥቶበት እየተከናወነ ያለ ተግባር መሆኑን በማንሳት ማህበረሰቡና ተቋማት ቆሻሻን ወደ ወንዝ ከመልቀቅ ሊታቀቡና መንግስት እያከናወነ ያለውን የወንዝ ዳርቻ ልማት ሊያግዙ ይገባል በማለት ገልፀዋል። የልደታ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሃፍቱ ብርሀኑ እንደተናገሩት የወንዝ ዳርቻዎችን በማልማትና ከበካይ ነገሮች በመከላከል ወንዞች የከተማችን ተጨማሪ የውበት ነፀብራቅ እንጂ የጤና ጠንቅ እንዳይሆኑ መስራት ይኖርብናል ብለዋል። መንግስት ከተማችንን ውብ ፅዱና ለነዋሪዎች እንዲሁም ለጎብኝዎች ምቹ ለማድረግ ከሚያከናውናቸው ተግባራት አንዱ የወንዝ ዳርቻ ልማትና ወንዞችን ከብክለት የመከላከል ተግባር መሆኑን የገለፁት አቶ ሃፍቱ ማህበረሰቡም ሆነ ተቋማት ወንዞችን በመጠበቅ ረገድ የድርሻቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል። የክ/ከተማው የአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንተነህ በፍቃዱ የወንዝ ዳርቻዎችን የማልማት ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀው ማህበረሰቡ ወንዞችን ከባይ ነገሮች በመጠበቅ አገራዊ ግዴታውን ሊወጣ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል። አቶ አንተነህ አክለውም የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ እና የቁጥጥርና የክትትል ስራን ማጠናከር በትኩረት ይሰራበታል ብለው ግንዛቤ ተፈጥሮላቸው ላልታረሙ ተቋማትና ግለሰቦች በደንቡ መሰረት እንደሚቀጡ ገልፀዋል። ተሳታፊዎች በበኩላቸው የወንዞችን ንፅህና መጠበቅ ጤናማ የሆነ ማህበረሰብ ለመገንባት ያስችላል ብለው የወንዞችን ንፅህና በመጠበቅና በማስጠበቅ ረገድ አመራሩ የድርሻውን ይወጣል ማህበረሰቡም አጋዥ ሊሆን ይገባል በማለት ተናግረዋል። የክ/ከተማው ደንብ ማስከበር ጽ/ቤትና አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ለደንብ ቁጥር 180/2017 ተፈፃሚነት በትጋት እንደሚሰሩም ተገልጿል።