የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ ቤት የመምህራን እና የተማሪዎች ስፖርታዊ ሊግ ውድድር የማጠቃለያ ፕሮግራም አካሄደ።
የልደታ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት የ2017 የትምህርት ቤቶችና "የመምህራን ስፖርት ሊግ ውድድር የትምህርት ቤቶች ስፖርት ሊግ ውድድርን ባህል በማድረግ ጤናማ ንቁና ብቁ ትውልድ እንፈጥራለን" በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ የመዝጊያ ፕሮግራም ተካሄደ
የልደታ ክፍለ ከተማ የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሰፋ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች፤ የምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች ፣የከተማና የክፍለ ከተማ ባለሙያዎች መምህራን, በተጨማሪም ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።
ስፖርት ለጤና፣ ለአንድነት፣ ለመቻቻል እና ፍቅርን ለማጎልበት ያለው ሚና የጎላ ሲሆን የነገ ሀገር ተረካቢ በሆኑት ተማሪዎች ውድድር መጀመሩ የሚበረታታ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ተገልጿል
ስፖርት በአእምሮ የዳበረና በስነ ምግባር የታነፀ ጤናው የተጠበቀ ትውልድ ከማፍራትም ባሻገር የእርስ በእርስ ግንኙነትን ለማጠናከር ይጠቅማል በማለት ገልፀዋል።
በክላስተር 1 እና በክላስተር 2 ሲካሄድ የነበረው የመምህራን የእግር ኳስ ውድድር በክላስተር 2 6 ለ1አሸናፊነት ተጠናቋል።
በመጨረሻም በውድድሩ ተሳታፊ ለነበሩትና ለአሸናፊዎች የዋንጫ የሰርተፍኬትና የሜዳልያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።