• የልደታ አስተዳደር ህንፃ 2ኛ ወለል ቢሮ ቁጥር 205
  • +251912689710
  • ዓርብ, ህዳር 14, 2016 ዓ.ም

image
image
image
image
image

የልደታ ክፍለ ከተማ የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።

የካቲት 29, 2017
"ስነ-ምግባር እና መልካም አስተዳደር ለተሻለ አገልግሎት" በሚል መሪ-ቃል ስልጠና የሰጡት የባለስልጣኑ የስነ-ምግባርና የፀረ ሙስና ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ ተቋሙ የመልካም አስተዳደር እና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የሚያስችል ስልጠና ሰጥተዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት በደንብ ቁጥር 180/2017 የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሰጠ ስልጠናው ኦፊሰሮች በስነ ምግባር በመታነፅ ነዋሪዎቻችን ላይ ደንብን ተግባራዊ ከማድረጋቸው በፊት ለማህብረተሰቡ ግንዛቤ በመፍጠር የቅድመ የመከላከል ሥራዎችን መስራት እንዳለባቸው ለማስገንዘብ ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና ነው በማለት የደንብ ኦፊሰር በስነ ምግባር በመታነፅ መልካም አስተዳደርን በመቅረፍ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባቸው ተገልጿል ። የልደታ ክፍለ ከተማ አካባቢ ጥበቃ በተሰጠው ሀላፊነት አካባቢን በተለይ የወንዝ ዳርቻዎችንን ከብክለት በመጠበቅ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ፋይዳ እንዲሰጡ ለማድረግ በቅንጅት መስራት ይጠበቅብናል በማለት ገልፀዋል በደንቡ ዙሪያ ግንዛቤ ተፈጥሮ ከአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመስራትና በትኩረት የተሰጠንን ሃላፊነት መወጣት ይጠበቅብናል ፡፡ በመድረኩ የተላለፍት መልዕክቶችን በመያዝና በመገንዘብ ለሚመለከታቸው አካላት ግንዛቤውን በመፍጠርና በማስጨበጥ የማህበረሰባችን ከደንብ መተላለፍ እንዲቆጠብ ማድረግ ይገባል በማለት ከብክለት ለመከላከል የሚያስችል ግንዛቤ አግኝተናል በማለት ተሳታፊዎች አንስተዋል። በመጨረሻም 2017 በጀት አመት የ6ወር አፈፃፃም የላቀ ውጤት ላስመዘገብ የእውቅናና ሽልማት ተሰጥቷል ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የ ልደታ ክ/ከተማ ኮሚንኬሽን ገፆችን ይከታተሉ !! http://linktr.ee/lidetacommunication1